RecordWell Data

በአማርኛ(PDF, 215KB)

Arlington County · Arlington County · Budget documents

Open the original document More from Arlington County

Text

Extracted automatically from the original. Tables and formatting may not survive; the original document is authoritative.

2026 የጠቅላላ ግዴታ ቦንድ ህዝበ ውሳኔዎች ኖቬምበር 3, 2026 English ሜትሮ እና ትራንስፖርት ጥያቄ፡ አርሊንግተን ካውንቲ ዕዳ በመውሰድና በከፍተኛው የዋና ገንዘብ መጠን $69,745,000 የሆነ የጠቅላላ ግዴታ ቦንዶችን በማውጣት፣ ከሌሎች ከሚገኙ ገንዘቦች ጋር በመሆን፣ ለዋሽንግተን ሜትሮፖሊታን አካባቢ ትራንዚት ባለስልጣንና ለሌሎች የትራንዚት፣ የእግረኛ፣ የመንገድ ወይም የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች የሚውሉ የተለያዩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ወጪ መሸፈን አለበት? ማብራሪያ፡ ይህ የውሳኔ ሀሳብ በመላው ካውንቲው ለሚገኙ የተለያዩ የትራንስፖርት፣ የመንገድ፣ የእግረኛ ማሻሻያና የትራንዚት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በዚህ የውሳኔ ሀሳብ ስር የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚችሉት የፕሮጀክቶቹ ግምታዊ ወጪዎች፡ ለአርሊንግተን ካውንቲ የWMATA / Metro የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም ድርሻ የተወሰነውን ክፍል ለመደገፍ $46.3 ሚሊዮን ዶላር፣ የአካባቢ ጎዳናዎችና መንገዶች ንጣፍን ለመስራት የሚወጣው ወጪ የተወሰነ ክፍል ለመደገፍ $15.0 ሚሊዮን፣ ለመንገድ መብራቶች $2.1 ሚሊዮን ዶላር፣ ለትራፊክ ምልክቶችና የዘመናዊ ትራንስፖርት ስርዓት ጥገና $1.8 ሚሊዮን፣ እንዲሁም ለሌሎች የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች $4.6 ሚሊዮን ዶላር ናቸው፡፡ የካውንቲው ቦርድ አስፈላጊ ወይም ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደሚሻሻለው በካውንቲው የካፒታል ማሻሻያ ዕቅድ ውስጥ ባሉ ሌሎች የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች መካከል የቦንድ ገንዘቦችን መልሶ ሊያከፋፍል ይችላል፡፡ የአካባቢ ፓርኮችና መዝናኛዎች ጥያቄ፡ አርሊንግተን ካውንቲ ከሌሎች ከሚገኙ ገንዘቦች ጋር በማጣመር ለሀገር ውስጥ ፓርኮችና መዝናኛዎች የሚሆኑ የተለያዩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ወጪ ለመደገፍ በከፍተኛው ዋና የገንዘብ መጠን $34,945,000 የብድር ውል በመግባት አጠቃላይ የዕዳ ግዴታ ቦንዶችን ማውጣት አለበት? ማብራሪያ፡ ይህ የውሳኔ ሀሳብ ለተለያዩ የፓርኮችና መዝናኛዎች ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በዚህ የውሳኔ ሀሳብ ስር የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚችሉት የፕሮጀክቶቹ ግምታዊ ወጪዎች፡ ለጌትዌይ ፓርክ $10.4 ሚሊዮን ዶላር፣ ለአርሊንግተን ቦትሀውስ ግንባታ $9.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ለድሩ ፓርክ ማሻሻያዎች $4.2 ሚሊዮን ዶላር፣ ለፓርኮች መሬት ግዢ እና ለሕዝብ ቦታ ፕሮግራም $3.0 ሚሊዮን ዶላር፣ ለመንገድና ድልድይ ዘመናዊነት $2.7 ሚሊዮን ዶላር፣ የተፈጥሮ የመቋቋም አቅምና ለተፈጥሮ መኖሪያነት እድሳት $1.3 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ለሌሎች የፓርኮች እና መዝናኛዎች ፕሮጀክቶች $3.8 ሚሊዮን ዶላር ናቸው፡፡ የካውንቲው ቦርድ አስፈላጊ ወይም ተገቢ ሆኖ ሲያገኘው፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚሻሻለው የካውንቲው የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም ውስጥ ላሉ ሌሎች የፓርኮችና መዝናኛዎች ፕሮጀክቶች የቦንድ በጀቱን እንደገና ማደል ይችላል፡፡ የማህበረሰብ መሰረተ ልማት ጥያቄ፡ አርሊንግተን ካውንቲ ከሌሎች ከሚገኙ ገንዘቦች ጋር በማጣመር የተቋማት የካፒታል ጥገናን፣ የተቋማት ንድፍና ግንባታን፣ የአርሊንግተን አጎራባች ሰፈሮች ፕሮግራምንና ሌሎችንም የካውንቲውን መሰረተ ልማቶች ጨምሮ የበርካታ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ወጪ ለመደገፍ በከፍተኛው ዋና የገንዘብ መጠን $58,825,000 ዶላር የብድር ውል በመግባት አጠቃላይ የእዳ ግዴታ ቦንዶችን ማውጣት አለበት? ማብራሪያ፡ ይህ የውሳኔ ሀሳብ ለተለያዩ የካውንቲው የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በዚህ የውሳኔ ሀሳብ ስር የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚችሉት የፕሮጀክቶቹ ግምታዊ ወጪዎች፡ ለቦልስተን የህዝብ መኪና ማቆሚያ ህንፃ $10.0 ሚሊዮን ዶላር፣ ለአስፈላጊ የሲስተም መሰረተ ልማቶች $9.3 ሚሊዮን ዶላር፣ የተቋማት ጥገና ፕሮግራም $8.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ለአርሊንግተን ማዕከላዊ ቤተመጽሐፍት $7.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ለካውንቲው የቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶች $7.2 ሚሊዮን ዶላር፣ ለማረሚያ ቤት (ማቆያ) $6.6 ሚሊዮን ዶላር፣ ለአርሊንግተን አጎራባች ሰፈሮች ፕሮግራም $2.0 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ለሌሎች የካውንቲው የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች $7.7 ሚሊዮን ዶላር ናቸው፡፡ የካውንቲው ቦርድ አስፈላጊ ወይም ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደሚሻሻለው በካውንቲው የካፒታል ማሻሻያ ዕቅድ ውስጥ ባሉ ሌሎች የካውንቲውና የማህበረሰብ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል የቦንድ ገንዘቦችን መልሶ ሊያከፋፍል ይችላል፡፡ 2026 የጠቅላላ ግዴታ ቦንድ ህዝበ ውሳኔዎች ኖቬምበር 3, 2026 English መገልገያዎች ጥያቄ፡ አርሊንግተን ካውንቲ ከሌሎች ከሚገኙ ገንዘቦች ጋር በማጣመር የአርሊንግተን ካውንቲ የውሃ ብክለት መቆጣጠሪያ ጣቢያንና ለካውንቲው አገልግሎት የሚሰጡትን የውሃና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን ዲዛይን የማውጣት፣ የማስፋፋት፣ የማሻሻያና የእድሳት ወጪዎችን ለመደገፍ በከፍተኛው የገንዘብ መጠን $20,745,000 የብድር ውል በመግባት አጠቃላይ የዕዳ ግዴታ ቦንዶችን ማውጣት አለበት? ማብራሪያ፡ ይህ የውሳኔ ሀሳብ ለካውንቲው የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ፣ የውሃና የፍሳሽ መስመሮች መሰረተ ልማት ከፍተኛ ማሻሻያዎች የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በቦንድ ገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚችሉት የፕሮጀክቶቹ ግምታዊ ወጪዎች፡ ለዋሽንግተን አኳዳክት ስርዓት የካፒታል ማሻሻያዎች $10.2 ሚሊዮን ዶላር፣ ለውሃ ዋና መስመሮች መተኪያ ፕሮግራም $8.0 ሚሊዮን ዶላር፣ ለውሃ ማጠራቀሚያ እድሳት $1.5 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ለትሬድስ ሴንተር እቃዎችና ማሻሻያዎች $1.0 ሚሊዮን ዶላር ናቸው፡፡ የካውንቲው ቦርድ አስፈላጊ ወይም ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደሚሻሻለው በካውንቲው የካፒታል ማሻሻያ እቅድ ውስጥ ባሉ ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች መካከል የቦንድ ገንዘቦችን መልሶ ሊያከፋፍል ይችላል፡፡ አርሊንግተን የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ጥያቄ፡ አርሊንግተን ካውንቲ ከሌሎች ከሚገኙ ገንዘቦች ጋር በማጣመር ለአርሊንግተን የህዝብ ትምህርት ቤቶች የሚሆኑ የተለያዩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ወጪ ለመደገፍ በከፍተኛው ዋና የገንዘብ መጠን $80,000,000 የብድር ውል በመግባት አጠቃላይ የዕዳ ግዴታ ቦንዶችን ማውጣት አለበት? ማብራሪያ፡ ይህ የውሳኔ ሀሳብ ለአርሊንግተን የህዝብ ትምህርት ቤቶች የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም የሚሆኑ ገንዘቦችን ያቀርባል፡፡ በዚህ የውሳኔ ሀሳብ ስር የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው የፕሮጀክቶቹ ግምታዊ ወጪዎች፡ • የጄምስታውን መደብኛ ትምህርት ቤት ማደሻ ($29,000,000) • የኦክሪጅ መደብኛ ትምህርት ቤት ማደሻ ($31,000,000) • ዋና መሰረተ ልማት – የህንፃ ስርአቶች ($20,000,000) የትምህርት ቦርዱ አስፈላጊ ወይም ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደሚሻሻለው በትምህርት ቦርዱ የካፒታል ማሻሻያ ዕቅድ ውስጥ ባሉ ሌሎች በትምህርት ቤት ፕሮጀክቶች መካከል የቦንድ ገንዘቦችን መልሶ ሊያከፋፍል ይችላል፡፡

Source: Arlington County website. First collected Oct 27, 2026.